ዩክሬን በሁለት የሩሲያ መርከቦች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን በክረሚያ ግዛት በሚገኘው የጥቁር ባህር ላይ በወሰደችው የአየር ጥቃት አዞቭ እና ያማል የተባሉ ሁለት የሩሲያ መርከቦችን መምታቷን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል፡፡
ከመርከቦቹ በተጨማሪ የሩሲያ የባህር ኃይል በጥቁር ባህር ውስጥ የሚጠቀመበትን የመገናኛ ማእከል እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች መውደማቸውን ነው የዩክሬን ጦር ያስታወቀው፡፡
የክረሚያ ባለስልጣናት በበኩላቸው ÷ ዩክሬን ሴባስቶፖል በተባለው የክረሚያ ወደብ ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ገልፀው በጥቃቱ የሩሲያ ባህር ሀይል መልዕክት መላላኪያ የሆነው የቴሌግራም መተግበሪያና የህዝብ መጓጓዣ ጀልባዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡
“በጥቃቱ በአካባቢው ከነበሩ ስድስት ጀልባዎች አምስቱ መሰኮቶቻቸው ተሰባብረዋል፣ነገር ግን የተጉዱ ጀልባዎች በእለቱ ጥገና ተደርጎላቸዋል” ብለዋል ባለስልጣናቱ፡፡
ጥቃቱን ለመከላከል የሩሲያ ባህር ሀይል በወሰደው የአፀፋ ጥቃት ከ10 በላይ የሚሆኑ የዩክሬን ሚሳኤሎችን መትቶ መጣሉን ዘቴሌግራፍ አስነብቧል፡፡