በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡
በቻይና ሁዋን ከተማ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ማሬ ዲባባ ርቀቱን 2 ሰዓት 25 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡
በተመሳሳይ በጣልያን ሚላኖ ከተማ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት አንችናሉ ደሴ 1 ሰዓት 07 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት አሸንፋለች፡፡
በቻይና ቼንግዱ በተካሄደ የወንዶች ማራቶን ውድድር አትሌት ፈቃዱ መርጋ ርቀቱን በ2 ሰዓት 16 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሲያሸንፍ÷ አትሌት በለጠ መኮንን ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በሌላ በኩል በቻይና ውዢ ከተማ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ታዱ አባተ ርቀቱን 2 ሰዓት 6 ደቃቃ ከ18 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸንፏል፡፡
በዚሁ ርቅት አትሌት አባይ አለሙ ውድድሩን 2 ሰዓት 6 ደቀቂ ከ50 ሰከንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል፡፡
በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በተካሄደ የ8 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርም በሪሁን ፈዬ 1ኛ፣ ገመቹ ቶለሳ 2ኛ እና አየንሳ አለሙ ደግሞ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡