Fana: At a Speed of Life!

የቲቢ በሽታን ለመግታት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቲቢ በሽታን ለመግታት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዓለም የቲቢ ቀን በኢትዮጵያ ለ27ኛ ጊዜ “በእርግጥም የቲቢ በሸታ ሥርጭትን መግታት እንችላለን” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በሚንስቴሩ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ የቲቢ በሽታን ለመግታት በርካታ ሥራዎችን እየተተገበሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ቲቢ አሁንም የማኅበረሰቡ ችግር በመሆኑ በሽታውን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሽታው በከፍተኛ ደረጃ ከተሰራጨባቸው 30 የዓለም ሀገራት አንዷ መሆኗንም ጠቅሰዋል፡፡

ሚኒስቴሩ እና አጋሮቹ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩባቸው ከሚገኙ የጤና ፕሮግራሞች መካከልም የቲቪ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር አንዱ ነው ማለታቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2030 ቲቢን ጨምሮ የስጋደዌ እና ሌሎች የሳንባ በሽታዎችን ለመግታት ይፋ የሆነውን ሀገራዊ መሪ ዕቅድ ለማሳካት በቀጣይ 7 ዓመታት በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸው÷ ለዕቅዱ ስኬትም ባለድርሻ አካላት እና አጋር ድርጅቶች ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.