ኮይካ በክህሎት ልማት ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ(ኮይካ) በክህሎት ልማት ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ÷ በደቡብ ኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶንግ ሆ ኪም የተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ኮይካ በኢትዮጵያ የክህሎት ልማቱን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እና የቀጣይ የትብብር መስኮችን ተመልክተዋል፡፡
በውይይቱ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እንደገለጹት ÷ ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የቆየ የወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው፡፡
ኮይካ በኢትዮጵያ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እየሰራ ያለው ሥራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል፡፡
የኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶንግ ሆ ኪም በበኩላቸው እንዳሉት ÷ ሀገራቱ ያላቸውን የወዳጅነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማሳደግ እንፈልጋለን፡፡
ኤጀንሲው በክህሎት ልማቱ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ ይቀጥላልም ማለታቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማም የልዑካን ቡድኑ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡