Fana: At a Speed of Life!

ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት 21ኛ ዙር ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በውድድሩም ጉታኒ ሻንቆ 1ኛ፣ ብርነሽ ደሴ 2ኛ እና መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

መነሻ እና መድረሻውን አትላስ ሆቴል አካባቢ ያደረገው የሩጫ ውድድር÷ “የሴቶችን አቅም እንደግፍ ለውጥን እናፋጥን” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በዚህ ውድድር÷ አትሌቶች፣ የጤና ሯጮች እንዲሁም አምባሳደሮች ተሳትፈዋል፡፡

ለ1ኛ ደረጃ 70 ሺህ ብር፣ ለ2ኛ ደረጃ 45 ሺህ ብር እንዲሁም ለሦስተኛ ደረጃ 30 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.