ሚኒስትሯ እስራኤል ባለፈው ጥር ወር ላይ በጋዛ ከሚገኙት 13 ሺህ የኤጀንሲው ሰራተኞች ውስጥ 12ቱ በሃማስ ጥቃት ተሳትፈዋል በሚል መክሰሷን አስታውሰዋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ አውስትራሊያ ከሌሎች በርካታ ሀገራት ጋር በመሆን ለተመድ የእርዳታ ስራዎች ኤጀንሲ ምስራቅ አቅራቢያ ለፍልስጤም ስደተኞች መጠለያ ታደርግ የነበረውን የገንዘብ ድጋፍ አቋርጣ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
ድርጅቱም ባደረገው ማጣራት እስራኤል ባቀረበችው በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውንጀላ መሠረት የተወሰኑ የኤጀንሲው ሰራተኞችን ማባረሩን አመላክተዋል፡፡
ዎንግ ሀገራቸው ተይዞ የቆየው ስድስት ሚሊየን የካናዳ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ በፍጥነት እንደሚለቀቅ፣ ለዩኒሴፍ ተጨማሪ የ4 ሚሊየን ዶላር እና የ2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ደግሞ ለተመድ የጋዛ ተቋም ልዩ ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ከአውሮፕላን ምግብ ለመልቀቂያ የሚያገለግል 140 ፓራሹት ለዮርዳኖስ እና ለተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንደምትሰጥ መግለጻቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት ስዊድን፣ ካናዳ እና የአውሮፓ ህብረት የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ በተወሰነ ደረጃ እንደቀጠሉ የተናገሩት የድርጅቱ ኃላፊ፤ ሌሎች ለጋሾችም በቅርቡ ድጋፋቸውን ይቀጥላሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው መናገራቸውንም ጠቁሟል።