በአራት በመቶ ነፃ ቀዘፋ የውሃ ዋና ውድድር ኢትዮጵያ 4ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ጨዋታዎች በሴቶቹ ዘርፍ በተደረገው የአራት በመቶ ነፃ ቀዘፋ የውሃ ዋና ውድድር ኢትዮጵያ 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
አትሌቶቹ ርቀቱን ለመጨረስ 5 ደቂቃ 18 ሴኮንድ ከ96 ማይክሮ ሴኮንድ ወስዶባቸዋል።
ግብፅ በርቀቱ የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በማሻሻል የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፤ አልጄሪያ እና ዚምባቡዌ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል።