ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የማህበራዊና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ጉባኤ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የማህበራዊና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ጉባኤው የማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ከጤና ባሻገር በሚል መሪ ቃል እተካሄደ ሲሆን፥ ከነገ በስቲያ ይጠናቀቃል።
የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በዚህ ወቅት እንዳሉት በማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት በጤናው ዘርፍ ከእናቶችና ህፃናት ሞት ቅነሳ እንዲሁም ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤት ቢመዘገብም አሁንም ያልተፈቱ የጤና ችግሮች መኖራቸውን አንስተዋል።
ችግሮቹን ለመፍታትም በተዋረድ ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና ጤና ተቋማት በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል።
በጉባኤው ጥናታዊ ጽሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን፥ አነቃቂ ንግግሮች እና የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በተጨማሪም በእነዚህ ቀናት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሚከናወኑ ጥናታዊ ምርምሮች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚተገበሩ የተግባቦት ስራዎች ጋር የማጣመር፣ የመፈተሸና ለበለጠ ለስኬት የማዘጋጀት አቅጣጫ ይቀመጣል።