Fana: At a Speed of Life!

መስተዳድር ምክር ቤቱ የ77 ፕሮጀክቶችን ጥያቄ መርምሮ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ77 ፕሮጀክቶችን ጥያቄ መርምሮ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱ 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን በሆሳዕና ከተማ እያካሔደ ነው ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ በክልሉ 141 ፕሮጀክቶች ለመስተዳድር ምክር ቤቱ የቀረቡ ሲሆን ከቀረቡት ፕሮጀክቶች ውስጥ የ 77ቱን ፕሮጀክቶች ጥያቄ መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ቀሪዎቹ 35ፕሮጀክቶች ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርት ሲያሟሉ አስፈላጊውን የማጣራት ስራ በማከናወን በቀጣይ ውሳኔ እንደሚሰጣቸውና 29ኙ ደግሞ ውድቅ መደረጋቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በምክር ቤቱ ውሳኔ ያገኙት በኢንዱስትሪ እና አገልግሎት ዘርፎች የቀረቡ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.