ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡
የዩናይትድን የማሸነፊያ ጎሎች ማርከስ ራሽፎርድ እና ቡሩኖ ፈርናንዴዝ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል፡፡
ሁለቱም የፍፁም ቅጣት ምቶች በአርጀንቲናዊው የመስመር አጥቂ ጋርናቾ የተገኙ ሲሆን÷ በውድድር ዓመቱም ለክለቡ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምት ያስገኘ ብቸኛ ተጫዋች ሆኗል፡፡
የ28ኛ ሣምንት መርሐ-ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ምሽት 2፡30 የዋንጫ ተፎካካሪው አርሰናል በሜዳው ብረንት ፎርድን ያስተናግዳል፡፡