በጋዛ ከአውሮፕላን የተለቀቀ የምግብ ጥቅል ወድቆባቸው አምስት ሰዎች ሲሞቱ 10 መቁሰላቸው ተሰማ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓራሹት መዘርጋት ባለመቻሉ በጋዛ ከአውሮፕላን የተለቀቀ የምግብ ጥቅል ወድቆባቸው አምስት ሰዎች ሲሞቱ 10 መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡
አንድ የዓይን እማኝ እንደተናገሩት፤ እንደ ሮኬት እየተምዘገዘገ የመጣ የምግብ ጥቅል በአል-ሻቲ የስደተኞች መጠለያ አቅራቢያ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ጣሪያ ላይ መውደቁን ተናግረዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ጋዛ ከተማ አል ሺፋ ሆሰፒታል ተወስደው ድንገተኛ ክፍል መግባታቸውን የሆስፒታሉ የነርሶች ኃላፊ መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡
በሰሜን ጋዛ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቤታቸው ፍርስራሽ ስር፣ ያለ ውሀ፣ ኤሌክትሪክ እና ሌሌች መሠረታዊ አገልግሎቶች ለረሃብ ተጋልጠው እንደሚኖሩ ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!