Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት በሳምንቱ መጨረሻ ለጋዛ በባህር መተላለፊያ ዕርዳታ ማቅረብ እንደሚጀመር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ ከቆጵሮስ ለጋዛ በባህር መተላለፊያ ዕርዳታ ማቅረብ እንደሚጀመር የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ገልጸዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንቷ ይህንን ያስታወቁት አሜሪካ በጋዛ ጊዜያዊ ወደብ ለማቋቁም ያቀረበችው ሀሳብ ትችት ከገጠመው በኋላ ነዉ።
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከጋዛ ህዝብ ሩብ ያህሉ በረሃብ አፋፍ ላይ እንደሚገኝ እና ህፃናትም በረሃብ እየሞቱ መሆኑን ገልጿል።
 
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ዕቅዱን በደስታ እንደሚቀበል እና ሌሎች ሀገራትም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አስተላልፏል።
 
በጋዛ የሚቀርበው እርዳታ ተደራሽ የሚደረገው የእስራኤል የደህንነት ፍተሻዎች መስፈርቶችን መሰረት ያደረገ ሂደትን ካለፈ በኋላ እንደሆነ ተገልጿል።
 
እስራኤል ዕርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ እንቅፋት ሆናለች መባሉን በማጣጣል የእርዳታ ድርጅቶችን እርዳታ ማከፋፈል ባለመቻል ወቅሳቸዋለች።
 
በቆጵሮስ ንግግር ያደረጉት ቮን ደር ሌየን ጋዛ የሰብአዊ አደጋ እየደረሰባት እንደሆነ ጠቅሰው፤ የባህር መተላለፊያው ከፍተኛ መጠን ያለው ተጨማሪ እርዳታ ለማድረስ ያስችላል ብለዋል።
 
የእርዳታው ጭነት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ከዓለም ማዕከላዊ የማዕድ ቤት እርዳታ ድርጅት ጋር በመተባበር እንደሚቀርብ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.