Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ግዛቴ ካልተጣሰ በቀር ኒውክሌር አልጠቀምም አለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የግዛቷ ህልውና አደጋ ላይ ካልወደቀ በስተቀር የኒውክሌር የጦር መሳሪያ አልጠቀምም ስትል ገለጸች፡፡

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሐሙስ ለፌዴራል ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፥ ቀደም ሲል ሩሲያን ለመቆጣጠር የተደረጉት ሙከራዎች በሙሉ መክሸፋቸውን አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይ ግን ወራሪዎች በራሳቸው ላይ የሚያመጡት መዘዝ ሊታሰብ ከሚችለው በላይ የከፋ እንደሆነ በመግለጽ አስጠንቅቀዋል።

አክለውም፥ ምዕራባውያን ባይረዱትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚሄደው ንግግራቸው ሁሉን አቀፍ የሆነ የኒውክሌር ጦርነት ውስጥ እየገቡ ነው ሲሉም የማስጠንቀቂያ ንግግራቸውን አሰምተዋል።

ሞስኮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ወደ ህዋ ልታሰማራ ነው የሚለውን የምዕራባውያን ሚዲያ ዘገባዎች “መሠረተ ቢስ” ሲሉ አጣጥለውታል።

ይህም አሜሪካ ሩሲያ ላይ ጫና ለመፍጠር የሸረበችው ሴራ እንደሆነም ነው የጠቆሙት፡፡

ፑቲን፥ ባለፈው ሰኔ ወር ባደረጉት ንግግርም ኒውክሌር ሩሲያ ራሷን የምትከላከልበት መሳሪያ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

የሩሲያ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ትናንት በሰጡት መግለጫ፥ ሩሲያ በኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም ላይ ያላትን አቋም አብራርተዋል፡፡

በዚህም፥ ሩሲያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን የምትጠቀመው ግዛቷ ሲጣስ ብቻ እንደሆነ መግለጻቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

ሆኖም ግዛቷ በመጣስ ጥቃት ቢደርስባት በኒውክሌር ጦር መሳሪያ አጸፋውን ለመመለስ እንደማታመነታም ነው የተናገሩት፡፡

#Russia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.