ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዲቀበል ጥሪ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለአራተኛ ቀን በቀጠለው ድርድር ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዲቀበል ጥሪ አድርገዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በታላቁ የረመዳን ወር ሃማስ የጋዛን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲቀበል በትናንትናው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ስምምነቱ አሁን በሃማስ እጅ ነው በማለት ለስምምነቱ ድጋፍ ያሳዩ ሲሆን በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የእስራኤልን በጋዛ ጦርነት ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ባይደን እና ትራምፕ በእስራኤል ፍልስጤም ጉዳይ የተለያዩ ስለመሆናቸው የፖለቲካ ተንታኞች ሲገልፁ÷ ባይደን ለፍልስጤማውያን መጥፎ እንደነበሩ በማንሳት ትራምፕ ደግሞ የከፉ ይሆናሉ ብለዋቸዋል፡፡
የሃማስ እና የአሜሪካ ልዑካን በስድስት ሳምንታት የእርቅ ስምምነት ላይ ለመድረስ በካይሮ የኳታር እና የግብፅ አአሸማጋዮች ጋር እየመከሩ መሆኑ ተገልጿል።
የግብፅ አልቃሄራ ዜና አገልግሎት ድርጅት ድርድሩ ዛሬ ለአራተኛ ቀን እንደሚቀጥል መግለጹን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
በረመዳን የተኩስ አቁም ሊኖር ይገባል ያሉት ባይደን፤ ጦርነቱ በዚህ ወር የሚቀጥል ከሆነ ለእስራኤል በጣም አደገኛ ሊሆን ይችላል ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!