የእድሜ ባለጸጋዋ ሴት 117ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን አከበሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማርያ ብራኒያስ ሞሬራ የተባሉት የእድሜ ባለጸጋ ሴት 117ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን እያከበሩ እንደሆነ ተነግሯል።
የእድሜ ባለጸጋ ሴት በፈረንጆች መጋቢት 4 ቀን 1907 በሳን ፍራንሲስ ተወልደው በስምንተኛ ዓመት ዕድሜያቸው ላይ ወደ ስፔን ካታሎኒያ አቅንተው በዚያ እየኖሩ ይገኛል።
አዛውንቷ በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚገኙ የረጅም ዕድሜ ባለቤት ተብለው በጊነስ ወርልድ መዛግብት ላይ ስማቸው ሰፍሮ ይገኛል።
በጊነስ ወርልድ መዛግብት ላይ ስማቸው የሰፈረው የ118 ዓመት እድሜ ባለጸጋዋ ፈረንሳዊት ሉሲል ራንዶን በፈረንጆች ጥር 2023 ህይወታቸው ካለፈ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
ሞሬራ 117ኛ ዓመት ልደታቸውን በመልካም ጤንነት ላይ ሆነው ከቤተሰቦቻቸውና ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር ማክበራቸው ተነግሯል።
የእድሜ ባለጸጋዋ ሞሬራ የ80 ዓመት እድሜ ባላቸው ሴት ልጃቸው እገዛ ኤክስ (የቀድሞ ትዊተር) ማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡
በዚህ የትውተር አካውንታቸውም “እንኳን ለ117ኛው ዓመት ልደቴ አደረሰኝ” የሚል የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስፈራቸውን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡