Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካና ፊሊፒንስ የባህር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ፊሊፒንስ በደቡብ ቻይና ባህር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።
 
በቀጣናው ከቻይና ጋር ያለው ውጥረት እየከረረ በመጣበት በዚህ ወቅት አሜሪካ እና ፊሊፒንስ ወታደራዊ ልምምድ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል::
 
ዓመታዊ ወታደራዊ ልምምዱ በደቡብ ቻይና ባህር በሚገኙ የፊሊፒንስ ደሴቶች እና በተለያዩ ቁልፍ ቦታዎች እንደሚካሄድ ተመላክቷል።
 
የፊሊፒንስ ጦር ኮሎኔል ማይክል ሎጂኮ በሰጡት መግለጫ÷ ባሊካታን ወይም “ትከሻ-ለ-ትከሻ” በሚል የተሰየሙት ልምምዶች በሰሜናዊ እና ምዕራባዊ ክፍሎች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል።
 
ከዚህ ቀደም ከተደረጉ ልምምዶች የበለጠ ጠንካራ ልምምድ እንደሚካሄድ ጠቅሰው፤ ልምምዱ የሳይበር ደህንነት ስልጠና እና የመረጃ ጦርነት ላይ ያተኩራል ብለዋል፡፡
 
ለታይዋን በጣም ቅርብ የሆነችው ባታኔስ ደሴት ከልምምድ ስፍራዎች አንዷ ልትሆን እንደምትችልም ተናግረዋል፡፡
 
የመለማመጃ ስፍራዎቹ ሰንደቅ ዓላማችንን የምናውለበልብባቸው የፊሊፒንስ ድንበር አካል በመሆናችው ከአሜሪካ ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረጋችን ተፈጥሯዊ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
 
ፊሊፒንስ በዛሬው ዕለት የቻይና የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በደቡብ ቻይና ባህር በመርከቧ ላይ ለግጭት የሚዳርግ አደገኛ ክስተት ፈጽመውብኛል በማለት መክሰሷን ሬውተርስ ዘግቧል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.