በሰሜን ጋዛ ህጻናት በምግብ እጦት ለህልፈተ ህይወት እየተዳረጉ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ጋዛ ህጻናት በምግብ እጦት ለህልፈተ ህይወት እየተዳረጉ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለጹ፡፡
በጋዛ ዜጎች የረሃብ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ሀገራትን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየተነገረ ነው፡፡
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹትም፥ በጋዛ ህጻናት በምግብ እጦት ሳቢያ ለህልፈት እየተዳረጉ ነው፡፡
አያይዘውም፥ በሰሜን ጋዛ ሆስፒታሎች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፤ የነዳጅ፣ የምግብና የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት ችግሩን እንዳወሳሰበውም አንስተዋል፡፡
እስካሁንም አስር ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ለህልፈት መዳረጋቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ሆኖም በጋዛ የሚገኘው በሃማስ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ ካማል አድዋን በሚባል ሆስፒታል ቢያንስ 15 ህጻናት በምግብ እጥረት እና በቂ ውሃ ባለመውሰዳቸው (በድርቀት) መሞታቸውን አስታውቋል።
300 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ጥቂት ምግብና ውሃ ብቻ በጎጇቸው እንደሚኖርም ነው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ባለፈው ሣምንት በጋዛ ውስጥ ያለው ረሃብ አስከፊ መሆኑን በመግለጽ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ቢያንስ 576 ሺህ ሰዎች (ከህዝቡ አንድ አራተኛው) አስከፊ የምግብ እጦት እንዳጋጠመውም ነው የተነሳው፡፡
በሰሜን ጋዛ ከሚገኙት ከሁለት ዓመት በታች ከሆኑ ስድስት ህጻናት መካከል አንዱ በአስከፊ የተመጣጠነ ምግብ እጦት እየተሰቃየ መሆኑንም ገልጿል።
ዩኒሴፍ በበኩሉ፥ የፈራነው እየሆነ ነው ሲል በተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየደረሰ ስላለው የህጻናት ሞት ገልጿል።
ይህ የረሃብ አደጋ ሰው ሰራሽና የሚገመት ቢሆንም አስፈላጊው ትብብር ከተደረገ መቆጣጠር እንደሚቻል መገለጹን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
#Gaza #WHO #UN
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!