Fana: At a Speed of Life!

በዛምቢያ ሠራዊት ምክትል አዛዥ የተመራ ልዑክ የመከላከያ ሠላም ማሥከበር ማዕከልን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛምቢያ ሠራዊት ምክትል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ጄፌሪ ቾንጎ ዘየሴ የተመራ ልዑክ የመከላከያ ሠላም ማሥከበር ማዕከልን ጎበኝቷል፡፡

የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴና የማዕከሉ ጄኔራል መኮንኖች ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ የሰላም ማስከበር ማዕከሉ እና የማሰልጠኛ ተቋሙ እያከናወነ ያለውን ውጤታማ ስራዎች በማስመልከት አዎንታዊ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት በሰላም ማስከበር ያላት ውጤታማ ተሳትፎና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ለልዑካኑ ገለጻ መደረጉም ተገልጿል፡፡

ሜጄር ጄኔራል ጄፌሪ ቾንጎ ዘየሴ ባደረጉት ጉብኝት እንደተደሰቱና ጠቃሚና ልምድና ተሞክሮ ያገኙበት ጉብኝት እንደነበር መግለጻቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.