ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎው በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።
በሻምፒዮናው በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ፍሬወይኒ ሀይሉ 4:01.46 በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች።
በተመሳሳይ በሻምፒዮናው የሴቶች 800 ሜትር ውድድር ጽጌ ዱጉማ 2:01.90 በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች።