አሜሪካ ለጋዛ የመጀመሪያ ሰብዓዊ እርዳታ በአውሮፕላን ማቅረቧ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለጋዛ የመጀመሪያ ሰብዓዊ እርዳታ በአውሮፕላን ማቅረቧ ተገልጿል፡፡
የሰብዓዊ እርዳታው ከ30 ሺህ በላይ እሽግ ምግብ ሲሆን÷ በሶስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከአውሮፕላን በፓራሹት መቅረቡ ተመላክቷል፡፡
የእርዳታ አቅርቦቱ ከዮርዳኖስ ንጉሳዊ አየር ኃይል ጋር በጥምረት መከናወኑን የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።
ባለሥልጣናቱ እንደተናገሩት÷ አቅርቦቱ ዓርብ ዕለት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይፋ ካደረጉት ከብዙ ድጋፎች የመጀመሪያው ነው።
ሐሙስ ዕለት ህዝቡ በጭነት ተሽከርካሪዎች የቀረበለትን እርዳታ ለመቀበል ሲሮጥ በተወሰደ እርምጃ ቢያንስ 112 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ባይደን ዕርዳታውን ለማጠናከር ቃል መግባታቸው ተገልጿል።
ሲ-130 የተሰኙት የጦር አውሮፕላኖች በጋዛ የባህር ዳርቻ ከ38 ሺህ በላይ እሽግ ምግቦች ማራገፋቸውን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በሰጠው መግለጫው ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቀደም ሲል እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ግብፅ እና ዮርዳኖስን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት በጋዛ የምግብ እርዳታ በአውሮፕላን ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን÷ አሜሪካ ግን ይህ የመጀመሪያዋ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!