Fana: At a Speed of Life!

የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከየካቲት 25 ጀምሮ በልዩ መልኩ በዘመቻ ይሰጣል ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከየካቲት 25 እስከ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በልዩ መልኩ እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ታዳጊዎች በዘመቻ እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የእናቶች፣ አፍላ ወጣቶችና ህጻናት መሪ ስራ አስፈፃሚ የክትባት ቡድን አማካሪ አቶ ተመስገን ለማ÷ በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ስጋት የሆነው የማህጸን በር ካንሰር በገዳይነቱ በ2ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት ለቫይረሱ መፈጠር ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዝ ጠቁመው፤ የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከየካቲት 25 እስከ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በልዩ መልኩ እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ታዳጊዎች ብቻ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰጥ የነበረውን ክትባት አንድ ጊዜ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አማካሪው፤ ትምህርት ተቋማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫና የቅድመ መከላካል ስራ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ በዓመት በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት 5 ሺህ ሰዎች ህይወታቸው የሚያልፍ ሲሆን÷ እድሚያቸው ከ14 ዓመት በላይ ከሆኑት ሴቶች ከአምስቱ አራት የሚሆኑት በህይወት ዘመናቸው ለማህጸን በር ካንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.