ተቋርጦ የቆየው የደምቢ ዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ ዳግም ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ6 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የደምቢ ዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ወደ ደንቢዶሎ ከተማ በሳምንት ሦስት በረራዎች እንደሚደረጉም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
በረራው ዳግም መጀመሩም አየር መንገዱ በሀገር ውስጥ የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የማስፋፋት ሥራ አካል መሆኑ ተመላክቷል፡፡