የኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በሰመራ ከተማ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ) የኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሄደ።
በመጪው ሀምሌ ወር የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ ሀገራዊ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራት ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል።
መቀሌን መነሻ በማድረግ የተጀመረው ሀገራዊ ንቅናቄ በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በሲምፖዚየምና በተለያዩ የስፓርት ውድድሮች ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል።
በዚሁ የፍጻሜ የንቅናቄ ስነ- ስርአት ላይ አትሌት ኮማንደር ብርሃኔ አደሬ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ፣ አቶ ዳዊት አስፋው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ ፣ ወ/ሮ አሚና ሴኮ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በስነ -ስርአቱ ማጠናቀቂያም ኦሮሚያ ክልል ከአፋር ክልል የኦሎምፒክ ችቦ ተረክቧል።
በአፈወርቅ አበበ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!