Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በ500 የሩሲያ ተቋማት ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጣለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለሩሲያ ድጋፍ ያደርጋሉ ባለቻቸው 500 ተቋማት ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን÷ ማዕቀቡ የሩሲያውን ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አሌክስ ናቫሊ ሞት እና በነገው ዕለት ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አስመልክቶ የተጣለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በአሜሪካ ሴኔት ውሳኔ ምክንያት ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ ቢዘገይም ዋሽንግተን የምታደርገውን ያልተቆጠበ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለ ብለዋል፡፡

ለወደፊትም ሩሲያን በወጭ እና በገቢ ንግድ ያግዛሉ ተብለው በተለዩ 100 ተቋማት ላይ አሜሪካ ማዕቀብ የምትጥል መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችበት ግጭትና የተቃዋሚዎች አያያዝ ዋጋ ያስከፍላታል ብለዋል።

በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ሩሲያ ሚኮሌይቭ፣ ሉሃነስክ፣ ዶነስክ፣ ዛፓሮዥያ፣ ኬርሰን፣ ካርኬቭ እና አዲቪካ የተባሉ ከተሞችን ይዛለች፡፡

በአንፃሩ ከምዕራባውያን እና አሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ የሚደረግላት ዩክሬን በሩሲያ ላይ ያደረገችው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ የከሸፈ ሲሆን የተተኳሽ እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች እጥረት እያጋጠማት እንደሚገኝ ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.