ለሕጻናት መልካም የእንቅልፍ ሰዓት ቢያደርጉ የሚመከሩ ነገሮች በጥቂቱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕጻናት ከምግብ ባልተናነሰ መልካም የሚባል እንቅልፍ እንዲተኙ ማድረግ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡
በዚህም ለሕጻናት መልካም የእንቅልፍ ሰዓት እንዲሆንላቸው፡-
• ሕጻናት ሁልጊዜ መተኛት ወይም ሸለብ ማድረግ ያለባቸው ብቻቸውን ነው፤
• ሕጻናት ሁልጊዜ ሲተኙ ወይም ሸለብ (ናፕ) ሲያደርጉ ደህንነቱ በተረጋገጠ መተኛ ወይም መጫወቻ ቦታ ይሁን፤
• ከእንቅልፍ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ድንገተኛ ክስተቶችን ለመከላከል አልጋቸውን በሚገባ ያንጥፉ፤
• ብርድ ልብሶችን፣ መጫወቻዎችን ወይም ትራሶችን ከአልጋቸው አካባቢ ያስወግዱ፤
• በፍጹም ልጆችን ከሌላ ሰው ጋር ወይም ቁሶች ጋር አብረው መተኛት የለባቸውም (የመተኛ ቦታዎችን ከሌላ ሰዎች ወይም ቁሶች ጋር የሚጋሩ ልጆች ከፍተኛ የመታፈን አደጋ አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላል፤
• ልጆችን በሆዳቸው እንዲተኙ አያድርጉ (ይህ ትንታ ሊፈጥርባቸው ይችላል፤ ለመተንፈስም ከባድ ሁኔታን ይፈጥርባቸዋል፤
• ልጆችን ቢችሉ በአዋቂዎች አልጋ፣ ሶፋዎች፣ ወንበሮች ላይ፣ የመኪና ውስጥ መቀመጫ ወንበሮች ላይ አያስተኙ (ጠንካራ ፍራሽ ያለውና የራሱ አንሶላ ባለው ደህንቱ በተረጋገጠ መተኛ ላይ እንዲተኙ ያድርጉ) ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ይመክራል፡፡