ዩኔስኮ በአፍሪካ ለትምህርት ዘርፍ የማደርገውን ድጋፍ አጠናክራለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ገለጸ።
የድርጅቱ የትምህርት ረዳት ዳይሬክተር ጄኔራል ቲፋኒያ ጄኒኒ በአፍሪካ አሁንም በርካታ ታዳጊ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
የትምህርት ጥራት ጉዳይ አሁንም ብዙ ጥያቄ የሚነሳበት መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ዩኔስኮም በአኅጉሪቱ በትምህርት ዘርፍ የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ-ነዋይ ስለሚፈልግ የአፍሪካ ኅብረት ኃላፊነቱን በመውሰድ ለዘርፉ የሃብት ማሰባሰብ ሥራ በትጋት እንዲሠራና ሌሎች አካላትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡