Fana: At a Speed of Life!

በወልቂጤና ሆሳዕና ከተሞች ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ እና ሆሳዕና ከተሞች ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ ፡፡

መድረኩ “ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሠላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ ነው ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከህዝቡ ጋር ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ለመድረስ የሚያስችል ውይይት መሆኑም ተመላክቷል።

በወልቂጤ ከተማ በተካሄደው መድረክ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ÷ በሆሳዕና ከተማ መድረክ በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበርያ ፅ/ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.