Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሦስተኛው የኢትዮ-ሩዋንዳ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ መጠናቀቁን አስመልክቶ ሀገራቱ በአምስት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ እና የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንስት ቢሩታ ፈርመውታል።

ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በአደጋ መቀነስና ማስተዳደር፣ በስፖርት፣ በፖለቲካና በኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ሀገራቱ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.