Fana: At a Speed of Life!

የ2016 የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ሥራ በድሬዳዋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ሥራ “የተቀናጀ ተፋሰስ ልማትና አረንጓዴ ልማት” በሚል መሪ ሐሳብ በድሬዳዋ አሥተዳደር በዋሄል ወረዳ ሀሎቡሳ ቀበሌ ተጀምሯል።

በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢብራሂ ዩሱፍ እና ሌሎች የአሥተዳደሩ አመራሮች የተፋሰስ ልማት ሥራውን አስጀምረዋል፡፡

በማስጀመሪያው ላይ አቶ ኢብራሂም ባደረጉት ንግግር÷ የዘንድሮው የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ሥራ የአርሶ እና የአርብቶ አደሩን ምርት እና ምርታማነት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.