አቶ ጥላሁን ከበደ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ለሚካሄደው 9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የዝግጅት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም “የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ይካሄዳል፡፡
ለከተሞች ፎረም በወላይታ ሶዶ የሚከናወነው የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነ መገለጹንም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡