የሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ፖሊዮን ጨርሰን እናጥፋ” በሚል መሪ ሐሳብ የ2016 ሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ለ12ኛ ጊዜ ተካሂዷል።
በስድስት የውድድር ዘርፎች 150 አትሌቶችን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች በውድድሩ ተሳትፈዋል፡፡
በ21 ኪሎ ሜትር የተካሄደውን የወንዶች ውድድር እንየው ንጋት በግል 1 ሠዓት ከ2 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡
እንዲሁም አሰፋ ተፈራ 1 ሠዓት ከ2 ከ47 ሰከንድ በመግባት 2ኛ፤ ደበበ ተካ ደግሞ 1 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ርቀት በሴቶቹ የተካሄደውን ውድድር ሙላት ተክሉ 1 ሠዓት ከ15 ደቂቃ ከ5 ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
በዚሁ የውድድር መርሐ-ግብር ከለልቱ ካያሞ 1 ሠዓት ከ15 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ በመግባት 2ኛ እንዲሁም ፀግነሽ መኮንን 1 ሠዓት ከ15 ከ24 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በስምንት ኪሎሜትር የሴቶች ውድድር ወርቅነሽ ሾኔዶ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ÷መዳኒት ለይኩን እና ሎሜ ጋቶሬ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በወንዶቹ ለማ መለሰ ሲያሸንፍ፣ደምሴ ደግሞ ሁለተኛ እና ፎካሮ ሾኔ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በወርቅነህ ጋሻሁን