Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ከሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በቅደም ተከተል ምላሽ ይሰጣል – አቶ ብናልፍ አንዷለም

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ከሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በማጤንና ሕብረተሰቡን በማሳተፍ በቅደም ተከተል ምላሽ እንደሚሰጥ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልልከ20 በላይ በሆኑ ዋና ዋና ከተሞች ህዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በወሊሶ ከተማ በተካሄደውና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባሳተፈው ህዝባዊ ውይይት የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች እያጋጠመ ያለውን የመሠረተ ልማት አለመሟላት፣ የሥራ አጥነትና የማህበራዊ ችግሮች እንዲሁም የሠላምና ፀጥታ መደፍረስን በማንሳት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፤ ጥያቄያቸውንም አቅርበዋል።

ውይይቱን የመሩት አቶ ብናልፍ አንዷለም ÷ ከህዝቡ የተነሱት ችግሮች የልማት፣ የዕድገት እና የፍትሃዊነት ችግሮች መሆናቸውን በመጠቀስ መንግስት እነዚህ ጥያቄዎች ከህዝቡ ጋር በመሆን ይፈታቸዋል ብለዋል።

የአካባቢውን ፀጋ መሠረት በማድረግና ሕብረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ የልማት ሥራ ለማከናወን በትኩረት እንደሚሰራም አንስተዋል፡፡

ከሕዝቡ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መንግስት ምላሽ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመው÷ ህዝቡም ከመንግስት ጎን እንዲቆም መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.