Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ ፡፡

ሕዝባዊ ውይይቱ “ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው ።

በውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር ጥላሁን ከበደ ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር )ን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።

ውይይቱ በዋናነት ሕብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ፣ የሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል ።

በአዳነች አበበ፣ መሳፍንት እያዩ እና ዘረዓያዕቆብ ያዕቆብ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.