በአዳማ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
በውይይት መድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር መክረዋል፡፡
መድረኩ የሕብረተሰቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ተረድቶ ለመፍታት እንዲሁም ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተጠቁሟል።