53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
በሻምፒዮናው በካሜሮን በሚካሄደው 23ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በጋና አክራ በሚካሄደው የመላው አፍሪካ ውድድር እንዲሁም በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶ ተለይተውበታል፡፡
በማጠናቀቂያ ፕሮግራሙ የሴቶች የምርኩዝ ዝላይ እና የሴቶች እና የወንዶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድደሮች እየተካሄዱ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡