Fana: At a Speed of Life!

በጋዛ አስከፊ ረሃብ መከሰቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነትን ተከትሎ በጋዛ ከባድ የረሃብ አደጋ መከሰቱ ተገልጿል፡፡
 
የዓለም ጤና ድርጅት÷በፍተሻ ቦታዎች በሚፈጠረው መዘግየት ሳቢያ ከፍተኛ የምግብ እጥረት በመኖሩ ለተጎጂዎች ማድረስ አለመቻሉን አስታውቋል።
 
የእርዳታ ሰራተኛዋ ሜርሲ ኮርፕስ በበኩሏ÷ጥቂት የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ መድረሱን ተከትሎ 2 ሰዎች በመጨናነቅ ታፍነው ሕይወታቸው ሲያልፍ መመልከቷን ለአልጀዚራ ተናግራለች።
 
በርካታ አስከሬኖች በራፋ ሲቀበሩ እንዳዩ የተናገሩት አንድ የሕክምና ባለሙያም ሟቾቹ የት እንደቆሰሉና ስማቸውን እንኳን እንደማያውቁ ገልጸዋል።
 
የእስራኤል ወታደሮች ካን ዮኒስ በሚገኘው አል-አማል ሆስፒታል በመግባት ዶክተሮች እና ተፈናቃዮች እንዲወጡ እየጠየቁ መሆኑንም የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ አስታውቋል።
 
ከፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ጀምሮ እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደች ባለው የአጸፋ እርምጃ 26 ሺህ 751 በላይ ዜጎች ለሕልፈት መዳረጋቸው ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.