Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የአፍሪካ ከተሞች መሪዎችና ከንቲባዎች የአመራርነት ሚና ማጎልበቻ ፎረም ላይ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

አቶ ኦርዲን በድሪ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ÷ሀረር ከተማ በፎረሙ ላይ መሳተፏ ከአፍሪካ ታላላቅ የከተማ ከንቲባዎች ጋር ልምድ ለመለዋወጥና ተሞክሮ ለመቅሰም ትልቅ አስተዋጽዖ አለው፡፡

ከፎረሙ የሚቀሰመው ልምድና ተሞክሮ በቀጣይ ሀረር ከተማ የጀመረችውን ዘርፈ በዙ የሰላም፣የልማት፣የመልካም አስተዳደር ስኬታማ ለማድረግ እንደሚያግዝም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ÷ከተማዋ ለቱሪዝም ምቹና በአፍሪካ ደረጃ በኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ የሚያስችሉ ልምድና ተሞክሮ እንደሚቀሰምበት መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.