Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያስመዘገበችው ስኬት የሚበረታታና ለአፍሪካ ብሎም ለሌላው ዓለም አርኣያ የሚሆን ነው – የፋኦ ዋና ዳይሬክተር

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለው ስኬት የሚበረታታ እና ለአፍሪካ ብሎም ለሌላው ዓለም አርኣያ የሚሆን ነው ሲሉ የተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኪዩ ዶንግዩን ገለጹ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተሸለሙት የከበረው የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያ ግብርና ምርታማነት ትኩረት ሰጥተው መስራታቸውን አንስተዋል፡፡

በተለይም በኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነት እንዲያድግ ያደረጉት ጥረት እና ያስገኙት ውጤት የሚደነቅ እና የሚበረታታ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

ለአፍሪካ የምግብ ዋስትና ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ መኖሩን ጠቁመው÷ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የስንዴ ምርታማነትን በማሳካትና ስንዴን ወደ ውጪ በመላክ በተግባር አሳይተዋል ብለዋል፡፡

 

በኢትዮጵያ ያለውን የሥንዴ ምርታማነት በአካል ተገኝተው እንደጎበኙ እና ውጤታማነቱን እንዳረጋገጡም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ የተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለውን የስንዴ ልማት መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.