Fana: At a Speed of Life!

ሲአይኤ እና ሞሳድ ከኳታር ባለስልጣናት ጋር በእርቅና እስረኞችን በለመለዋወጥ ጉዳይ ሊመክሩ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ማዕከላዊ የስለላ ኤጀንሲ (ሲአይኤ) ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ እና የእስራኤል የሞሳድ ኃላፊ ዴቪድ ባርኔያ በጋዛ የሚገኙ ምርኮኞችን ለማስፈታት እና ጦርነቱን ለማስቆም የሚያስችል ሁለተኛ ስምምነት ለማድረግ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን አብዱራህማን አልታኒ ጋር በጥቂት ቀናት ውስጥ በአውሮፓ እንደሚገናኙ ተገልጿል።

የግብፅ የስለላ ኃላፊ አባስ ካሚል ስብሰባውን እንደሚቀላቀሉ ተጠቁሟል፡፡

በሃማስ እና በሌሎች የፍልስጤም ታጣቂዎች በእስር ላይ የሚገኙትን ወደ 130 የሚጠጉ እስረኞችን ለማስፈታት የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር አሁንም በንቃት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ያለው ማንኛውም አዲስ ስምምነት የጦርነት ማስቆም ዓላማ እንዳለው ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

ቁልፍ አስታራቂዎቹ በእርቅና እስረኞችን በመለዋወጥ ጉዳይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እየሞከሩ ነው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ኳታር ከግብፅ ጋር በመሆን ለማስታረቅ እና የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ መግባቱን ለማረጋገጥ ድርድር ላይ ገብታለች።

በፈረንጆቹ ህዳር ወር የተደረሰው ስምምነት ለሳምንት ተኩስ እንዲቆምና በእስራኤል ለታሰሩ የፍልስጤም እስረኞች ምትክ ከ100 በላይ እስረኞች እንዲፈቱ እድል መፍጠሩ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.