Fana: At a Speed of Life!

በማሊ በወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሊ በወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተከሰተ የመደርመስ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራብ ኩሊኮሮ አካባቢ በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ ነው የተከሰተው፡፡

በአካባቢው የወርቅ ማዕድን አውጪዎች ሃላፊ የሆኑት ኦማር ሲዲቤ የአደጋውን ሁኔታ ሲገልጹ ፥ በጩኽት የጀመረ የምድር መንቀጥቀጥ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

አደጋው በተከሰተበት ወቅትም በማዕድን ማውጫው 200 ሰዎች እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡

አክለውም ፥ ፍለጋው በአሁኑ ወቅት እንደቆመና እስካሁን 73 አስከሬን መገኘቱም ቢጠቁሙም ፥ የማዕድን ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ባዬ ኩሊባሊ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት እስካሁን የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ነው፡፡

በዚህም የማሊ መንግስት ለሟች ቤተሰቦች እና ለማሊ ሕዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

በተጨማሪም በማዕድን ማውጫ ቦታ አቅራቢያ የሚኖሩ ማህበረሰቦች የደህንነት መስፈርቶችን እንዲያከብሩ እና ለወርቅ ማውጫ ስፍራ በተከለሉት ብቻ እንዲሰሩ አደራ ብሏል።

ሆኖም በዚህ የወርቅ ማዕድን ለማውጣት በሚጠቀሙት አስተማማኝ ያልሆነ ዘዴዎች ምክንያት ለመሰል አደጋዎች መጋለጥ በሀገሪቱ የተለመደ ነው ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.