ዶናልድ ትራምፕ በኒው ሐምፕሻየር ግዛት ተቀናቃኛቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለቀጣዩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ሆነው ለመመረጥ የሚያስችላቸውን ነጥብ እየሰበሰቡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ትራምፕ በኒው ሃምፕሻየር ብቸኛ ተቀናቃኛቸውን የሪፐብሊካን እጩ ኒኪ ሃሌይን ላይ ድል ማስመዝገባቸው ተሰምቷል።
የሪፐብሊካን እጩ እና ብቸኛ የትራምፕ ተቀናቃኟ ኒኪ ሃሌይን የቀድሞ የደቡብ ካሮሊና አስተዳዳሪ የነበሩ ናቸው፡፡
ውጤቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ባደረጉት የድል ንግግር ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን አመስግነው ፥በኒክ ሃሌይ እና ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ላይ የሥላቅ ንግግር አሰምተዋል፡፡
የሪፐብሊካን እጩ ተወዳዳሪዋ ኒክ ሃሌይ “በጣም መጥፎ ምሽት አሳልፈዋል” እና “አያሸንፉም” ሲሉ ነው የተናገሩት።
ዶናልድ ትራምፕ÷ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ እያንዳንዱን የሕዝብ ድምጽ በሚባል ደረጃ ማሸነፋቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
ምንም እንኳን ዶናልድ ትራምፕ እያሸነፉ ቢሆንም ሌሎች ግዛቶች ይቀራሉ ፤ አላበቃም፤ ውድድሩን እቀጥላለሁ ሲሉም ኒክ ሃሌይ ቃላቸውን እንደሰጡ አር ቲ ዘግቧል፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት የፍሎሪዳው ገዢ ሮን ዴሳንቲስ ራሳቸውን ከፕሬዚዳንታዊ ውድድር በማግለል ዶናልድ ትራምፕን እንደሚደግፉ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
ሮን ዴሳንቲስ ከ2024 ፕሬዚዳንታዊ ፉክክር ራሳቸውን ያገለሉት ዛሬ በተካሄደው በኒው ሃምፕሻየር ግዛት የመጀመሪያ ደረጃ ውድድር ሊደረግ ሁለት ቀናት ሲቀረው ነው፡፡
የፍሎሪዳው ገዢ ይህን ሃሳብ ያነሱት በትራምፕ በአዮዋ ካውከስ 30 በመቶ ነጥብ ሽንፈት ከገጠማቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደሆነም ነው የተጠቆመው።
#US
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!