Fana: At a Speed of Life!

በዓለም የመጀመሪያው የወባ ክትባት በካሜሮን መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም የመጀመሪያ ነው የተባለው የወባ ክትባት በካሜሮን መሰጠት ጀምሯል፡፡

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ÷ካሜሮን በየዓመቱ 6 ሚሊየን በላይ የወባ በሽታ ተጠቂዎችን ታስመዘግባለች፡፡

በወባ በሽታ ሳቢያም በፈረንጆቹ 2021 ብቻ በካሜሮን 13 ሺህ 839 በላይ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡

ከሟቾች ውስጥም አብዛኛዎቹ የአምስት ዓመት እድሜ በታች ህጻናት መሆናቸው ነው የተጠቆመው፡፡

በዛሬው ዕለት የተጀመረው የክትባት መርሐ ግብርም በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የወባ ሥርጭት ለመግታት ሚናው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ክትባቱ  ጂ ኤስ ኬ በተሰኘ የእንግሊዝ መድሃኒት አምራች ኩባንያ የተፈበረከ ሲሆን÷ በዓለም ጤና ድርጅትም እውቅና አግኝቷል፡፡

በክትባት መርሐ ግብሩ ለ249 ሺህ 133 በላይ ህጻናትን የክትባት አገልግሎት ለመስጠት መታቀዱም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.