በመዲናዋ ለከተራና ጥምቀት በዓላት ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩትን የከተራና የጥምቀት በዓላት ተከትሎ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል፡፡
በጥምቀት በዓል በርካታ ህዝብ ታቦታትን አጅቦ ከተለያዩ ቤተ-ክርስቲያናት ወደ ጥምቀተ ባህር የሚንቀሳቀስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ስለሆነም በትራፊክ ፍሰቱ ላይ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በጥምቀት በዓል በርካታ ህዝብ ታቦታትን አጅቦ ከተለያዩ ቤተ-ክርስቲያናት ወደ ጥምቀተ ባህር የሚንቀሳቀስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ስለሆነም በትራፊክ ፍሰቱ ላይ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተለይም በርካታ ህዝብ በሚታደምበት በጃን ሜዳ ከጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው እስኪመለሱ መንገዶቹ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
– ከ6ኪሎ አደባባይ እስከ 3ተኛ ሻለቃ ፈረንሳይ ለጋሲዬን መንገድ
– ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ በምንሊክ ሆስፒታል እስከ ቀበና አደባባይ
– ከምንሊክ ሆስፒታል እስከ 6 ኪሎ ታክሲ ተራ
– ከቅድስተ ማርያም ቤ/ክርስቲያን እስከ 6 ኪሎ፣
– ከ6ኪሎ እስከ መነን፣
– ከሀምሌ 19 እስከ ግብፅ ኢምባሲ፣
– ከቅድስተ ማሪያም መነጸር ተራ እስከ ጃንሜዳ፣
– ከግንፍሌ ድልድይ ምንሊክ ሆስፒታል ውስጥ ለውስጥ፣
– ከግንፍሌ መገንጠያ ምንሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣
– ከምኒሊክ ሆስፒታል የኋላ በር እስከ ቤላ መገንጠያ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳና በዙሪያው ተሽከርካሪ አቆሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ሲሆን÷አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትእዛዝ በመቀበል የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል፡፡