Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት አመራሮች ስልጠና እንዲሳካ ላደረጉ አካላት እውቅና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ዙሮች እና ማዕከላት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ ሲሰጥ የነበረው የመንግሥት አመራሮች ስልጠና እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷል፡፡

እውቅናና ምስጋናው የፀጥታ መዋቅር አመራሮችን ጨምሮ ለስልጠናው ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ነው የተሰጠው።

በአዲስ አበባ በተካሄደው የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ -ሥርዓት ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲው፣ የፌደራል እና የክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አቶ አደም ፋራህ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በየደረጃው ለሚገኙ ሁሉም አመራሮች የተሰጠው ስልጠና የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲመለሱ እና የኢትዮጵያ ብልፅግና በአጭር ጊዜ እንዲረጋገጥ ያግዛል ብለዋል።

የዕዳ ወደ ምንዳ ስልጠና በተለያዩ ምክንያቶች ከዚህ በፊት ከተሰጡ ስልጠናዎች እንደሚለይ ገልጸው÷ ለአብነትም በይዘትና በጥራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ3 አጀንዳዎች ላይ ስልጠና የሰጡበት በመሆኑ የሚሉትን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም በሁሉም ዕርከን ላሉ አመራሮች ተመሳሳይ ስልጠና የተሰጠበት መሆኑ፣ ኅብረብሄራዊ በሆነ መልኩ ለ4 ዙሮች መካሄዱ እና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ከፍ ያሉ ርዕሶች ላይ ማተኮሩ ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

በአመራሩ ዘንድም በሀገራዊ ራዕይ ላይ የአመለካከት አንድነት እንዲሰርፅ ማድረጉንም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.