Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ስምምነት የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ነው – አምባሳደሮች

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችዉ የመግባቢያ ስምምነት የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ስኬት መሆኑን በተለያዩ ሀገራት የኢትየጵያ አምባሳደሮች ገለፁ፡፡

አምባሳደሮቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለመግባቢያ ስምምነቱ ተገቢዉን ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በፓኪስታን የኢፌዲሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር እንዳሉት ፥ ስምምነቱ ዲፕሎማሲያዊ ጉዟችን የት እንደደረሰ ማሳያ ነው፡፡

በተመደቡባቸው ሀገራት ሆነ በአመቺ አማራጮች ተገቢ የዲፕሎማሲ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ደግሞ ያነሱት በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብዙነሽ መሰረት ናቸው፡፡

ስምምነቱ ዛሬ ላይ ዓለም ከዕለት ዕለት በአዳዲስ ክስተቶች እየተፈተነች ባለችበት ወቅት የባህር በር አልባ ሆኖ መቀጠል ያለውን ፈተና ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑንም ያስረዳሉ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ዲፕሎማሲያዊ ሂደት በዚሁ መንገድ እንዲቀጥል የባለብዙ ወገን ስራዎቹ እንደሚቀጥሉም አምባሳደሮቹ ገልጸዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.