Fana: At a Speed of Life!

ጆዜ ሞሪንሆ ከሮማ አሰልጣኝነታቸው ተባረሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጆዜ ሞሪንሆ ከሮማ አሰልጣኝነታቸው መባረራቸው ተሰምቷል፡፡
ለስንብታቸው የቡድኑ ውጤት ማጣት እና ከዳኞች ጋር የሚፈጥሩት አለመግባባት ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ሮማ በሴሪአው ካደረጋቸው የመጨረሻዎቹ ስድስት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በኮፓ ኢታሊያም በላዚዮ መሸነፉ አይዘነጋም፡፡
ሮማ አሁን ላይ በሴሪአው ከመሪው ኢንተር ሚላን በ22 ነጥቦች ርቆ ይገኛል፡፡
የጆዜ ሞሪንሆ መሰናበት ምናልባትም የስፖርቱ ባለስልጣናት እፎይታን እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል።
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በፈረንጆቹ 2023/24 የውድድር ዘመን አምስት ቀይ ካርዶችን ያገኙ ሲሆን÷ በ2022/23 የውድድር ዘመን ደግሞ ሶስት ቀይ ካርዶችን ማግኘታቸው ይታወሳል።
በፈረንጆቹ መጋቢት 2023 በሴሪአው የውድድር ዘመን ከየትኛውም ተጫዋች የበለጠ ቀይ ካርድ የተሰጣቸው አሰልጣኝ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.