Fana: At a Speed of Life!

የሀላባ ብሔረሰብ የታሪክ ፣ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም በመካሄድ ላይ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀላባ የዘመን መለወጫ የሴራ በዓል አካል የሆነው የሀላባ ብሔረሰብ የታሪክ፣ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ዛሬ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
 
የሀላባ የዘመን መለወጫ የሴራ በዓል “ሴራችን የአንድነት ማሳያ ድንቅ ምልክታችን” በሚል መሪ ሀሳብ በመከበር ላይ ነው።
 
የሀላባን የዘመን መለወጫ የሴራ በዓልን በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
 
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር÷ ኢትዮጵያ በርካታ ቅርሶች ያሏት ሀገር በመሆኗ በቀጣይም በቅደም ተከተል ሌሎች ሀብቶችን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
 
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሁዲን ሁሴን በበኩላቸው÷ በሀላባ ብሔረሰብ ለዘመናት ተጠብቀው የቆዩ በርካታ ባህልና ቅርሶችን ለሚቀጥለው ትውልድ እንዲሻገር ማድረግ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።
 
የሴራ በዓል ሀላባዎች መንገሳ ብለው በሚጠሩት የታህሳስ ወር ላይ የሚከበር ሲሆን÷በወሩ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ሲከበር መቆየቱም ተነስቷል።
 
በብርሃኑ በጋሻው
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.