የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ያሰለጠናችውን ከፍተኛ መኮንኖች እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ9ኛ ዙር በአጭር ኮርስ ያሰለጠናችውን ከፍተኛ መኮንኖች በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪና የተኩስ አመራር ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አለምእሸት ደግፌን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ከምረቃ መርሃ ግብሩ በኋላ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ የመሰረተ ልማት ግንባታና የፎቶ አውደ ርእይ እንደሚመረቅ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡