በሕገ-ወጥ መንገድ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ነጋዴዎች ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ተቀጡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት ባካሄደው ክትትልና ቁጥጥር ከ980 በላይ በሆኑ የንግድ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ አጀሊ ሙሳ እንዳሉት÷ በሕገ-ወጥ መንገድ የተንቀሳቀሱ፣ ንግድ ፈቃድ ሳያድሱ የተገኙ እና የንግድ ሥርዓቱን በተላለፉ ከ980 በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ እንደ ጥፋታቸው ደረጃ የተለያየ ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
የተወሰዱት እርምጃዎችም÷ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያን ጨምሮ በሕግ ተጠያቂ ማድረግን እና የንግድ ፈቃድ መሰረዝን እንዳካተተ አብራርተዋል፡፡
ከጥፋተኛ ነጋዴዎች በቅጣት የተገኘ 1 ሚሊየን 169 ሺህ 134 ብር ለመንግሥት ገቢ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!