Fana: At a Speed of Life!

ማይክሮሶፍት ኩባንያ የጋዜጠኞችን ተግባር በሮቦቶች ሊተካ ነው

አዲስ አበባ፣ግንቦት 22 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማይክሮሶፍት ኩባንያ ኤም.ኤስ .ኤን በተሰኘ ድረ ገጹ  ላይ በጊዜያዊነት ይሰሩ የነበሩ በርከት ያሉ  ጋዜጠኞችን በሮሆቦት ሊተካ መሆኑን አስታውቋል።

ኩባንያው እንደሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለመገናኛ ብዙሃን ገንዘብ በመክፈል ዘገባቸውን በድህረ ገጹ ላይ የሚያትም ሲሆን ÷በድረገጹ ላይ የትኞቹ ዘገባዎች መውጣት እንዳለባቸው የሚወስኑት ደግሞ  የቀጠራቸው ጋዜጠኞች እንደነበሩ ተነግሯል።

ጋዜጠኞቹ  ለኩባንያው ድረ ገጽ  ዜና  በማደራጀት፣ርዕስ በመስጠትና  እና ፎቶ በማስገባት ሲሰሩ  የነበሩ  መሆናቸው ተመላክቷል።

ከዚህ በኋላም ይህ ተግባር በሰው ሰራሹ አርተፊሻል ኢልተለጀንስ የሚተካ ይሆናል ነው የተባለው።

ጉዳዩን አስመልክቶ ማይክሮሶፍት በሰጠው መግለጫ“እንደማንኛውም ኩባንያዎች ሥራችንን በመደበኛነት እንገመግማለን፣ ውሳኔው የንግድ ግምገማችን አካል እንጂ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር የሚገኛኝ አይደለም ብሏል።

የኩባንያውን አዲሱ ውሳኔ ተከትሎ በሰኔ ወር መጨረሻ 50 በጊዜያዊነት የተቀጠሩ ሰራተኞች ስራቸውን ያጣሉ ተብሏል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.